Up next


Mezmur 'Yene Nardos' by Zerfe Kebede with Lyrics

113 Views
መዝናኛ
7
Published on 26 Jun 2020 / In Shows

Yene Nardos by Zemarit Zerfie Kebede.
This is an Ethiopian Orthodox hymn based on the Songs of Solomon.
የእኔ ናርዶስ በዘማሪት ዘርፌ ከበደ (ኦፈ ያሬድ)::
[በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን (መኃ) ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር::]

የእኔ ናርዶስ የእኔ ቤዛ
በመአዛው ልቤን ገዛ (መኃ 1:2)
ያንን መዳፍ ተመልክቼ
ተከተልኩት ሁሉን ትቼ (መኃ 5:4)
...
እንቅልፍ የለኝ በአልጋዬ
ፊቴ ታጥቧል በእንባዬ
በውድቅቱ ነቅቻለሁ
ውዴን ብዬ ወጥቻለሁ (መኃ 3:1)
አዝ.......
የሣሮኑ ጽጌሬዳ
ያገኘሁህ ምድረ በዳ (መኃ 5:8)
ስለፍቅርህ ታምሜአለሁ
በመስቀልህ ታክሜአለሁ
አዝ.......
ተራሮችን የዘለለ
አድማሳትን ያካለለ (መኃ 2:8)
ጥላው ሲሸሽ ወደማታ
ፍቅርህ ጠራኝ የእኔ ጌታ (መኃ 2:17)
አዝ.......
ግራው ሰላም አንተራሰኝ
ከሞት ነጥቆ ቀኙ አቀፈኝ (መኃ 2:6)
ውዴ የኔ እኔም የእርሱ
ማን ሊለየኝ ከንጉሡ (መኃ 2:16)
አዝ.......

Show more
Facebook Comments

Up next