ቀጥሎ የሚጫወተው

Reaction on funny videos part 1
መዝናኛ
16 ጊዜ ታይቷል

Geregera Keranyo Medhanealem Church Construction in Ethiopia (Part 6A)

13 ጊዜ ታይቷል
መዝናኛ
7
የተለቀቀበት ቀን 24 Sep 2019 / በ ሾው

ለተከበራችሁና ለተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገቻችን በሙሉ በድጋሚ እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በጤናና በህይወት አሸጋግሮ ለ2010 አዲስ አመት አደረሳችሁ:: ወደፊትም ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና ያድርሳችሁ እያልን ልባዊ የሆነ መልካም ምኞታችን በመግለጽ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችን እናቀርባለን::
ከእዚህ በመቀጠል በአንክሮት ልንገልጽ የምንወደው በቅድስት ሐገራችን ኢትዮጵያ በሰሜን ወሎ ሐገረ-ስብከት በላስታ ላሊበላ አውራጃ በመቄት ወረዳ በገረገራ ከተማ ከታሪካዊ አመሠራረቱ ጀምሮ የታላቁ ደብር :
ደ/ሐይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አካልና አጸድ(ቅጥር) በሆነው በድሮ መጠሪያ ስሙ አምባው ይባል በነበረው የአባ ሳሙኤ ዘዋልድባ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም ተራራማ ቦታ ላይ በአሁኑ ሰዓት በመሠራት ላይ የሚገኘው የገረገራ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም: አቡነ ተክለሐይማኖትና አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ እስከ አለፈው ነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም የመጀመሪያው ሳምንት የደረሰበትን ደረጃ በከፊል የሚያሳይ የክፍል ስድስትን( 6) ቪዲዮ መልዕክት በሁለት ተከታታይና ተያያዥ በሆኑ ንዑሳን ክፍሎች 'ሀ' እና 'ለ' ብለን በመክፈልና በእዚሁ ክፍል 6 (tስድስት) ሥር 'ለ' በሚል ርዕስ የጸበል ቤቶችን ግንባታ የሚያሳይ የቪዲዮ መልዕክት አከታትለን ያቀረብን ስለሆነ በማስተዋልና በመረጋጋት እንድትከታተሉትና የሚኖሯችሁን ገንቢ አስተያየቶች በመስጠት:ላይክና ሸር በማለትና ከእዚያም ባሻገር በሙያና በገንዘብ: በሃሳብና በጸሎት የምትችሉትን በመርዳት ለጀመርነው ትልቅ ሥራ መሳካትና መልካም ፍጻሜ ላይ መድረስ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ በማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታችሁን እየተወጣችሁ የእዚህ ባለብዙ ታሪክ ታላቅ ገዳም በረከት ተሳታፊዎች ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በትህትንና እናስተላልፋለን::
በገንዘብ ለመርዳት ለምትፈልጉ የባንክ አድራሻና ቁጥራችን
በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ስም (Under Keranyo Medhanealem EOTC Unity Church.)
In USA. Las Vegas City at Federal Credit Union
Acc.# 151120: በኢትዮጵያ አቪሲኒያ ባንክ መቄት ቅርንጫፍ የባ.ሂ.ቁ. 6000018 መሆኑን እየገልጻለን ::
ለሚኖሯችሁ ጥያቄዎችና ገንቢ አስተያየቶችም በስልክ ቁጥር (702) 202-7422 በመደወልና በ [email protected] ኢሜል በማድረግ አጥጋቢ መልስና ማብራሪያ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ ማረጋገጥ እንወዳለን::
ከእዚህ በፊትም ከጎናችን በመቆም
በሙያና በገንዘብ: በሃሳብና በጸሎት ከፍተኛ እገዛና ድጋፍ ላደረጋችሁልን ወገኖቻችን ሁሉ
በልዑል እግዚአብሔርና በገዳሙ ስም ላቅ ያለ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን::
በተረፈ ለሁላችንም መልካም አዲስ አመት ይሁንልን እንላለን ::

ከታላቅ የአክብሮት ሰላምታ ጋር :

በሐገር ውስጥና በውጭ አገር ያለው የገዳሙ ሕንጻ አሠሪ አስተባባሪ ኮሚቴ ::


Facebook Page: https://www.facebook.com/%E1%8....B%A8%E1%8C%88%E1%88%

ተጨማሪ አሳይ
ኮሜንት ፃፍ

ቀጥሎ የሚጫወተው

Reaction on funny videos part 1
መዝናኛ
16 ጊዜ ታይቷል