Up next


Sheger Werewoch - ጠንቋይዋ ከነባለቤቷ ተሰውራለች - የሸገር ወሬዎች

68 Views
shegerfm
1
Published on 27 Mar 2019 / In Entertainment

Sheger Werewoch - ጠንቋይዋ ከነባለቤቷ ተሰውራለች - የሸገር ወሬዎች በበየነ ወልዴ

የጠንቋይዋ ነገር…
ጠንቋይዋ ከነባለቤቷ ተሰውራለች…

ቦታው አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ ግሩም ሆስፒታል አካባቢ ነው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት አንዲት ሴት አንድን የዛን አካባቢ ነዋሪ ተጠግታ ሐብታም አደርግሃለሁ አለችው ይለናል ይህ የበየነ ወልዴ ዘገባ፡፡ እሱም፣ የአካባቢው ሰው እንደሚለው፣ የተገባለትን ተስፋ አድርጎ የሚኖርበትን የቀበሌ ቤት ለቅቆላት ኩሽና ውስጥ መኖር ጀመረ፡፡

ግን ደግሞ እንዳለችው ሐብታም አልሆነም፡፡ ሴትየዋም ቤቱን የጥንቁልና ማካሄጃ አደረገችው፡፡ በሴትየዋ ድርጊት በተናደዱ የአካበቢው ነዋሪዎች ግፊት እና እሱም የምኖርበት ኩሽና ጠቦኛል ሲል ቤቴን ልቀቂልኛ ማለት ጀመረ፡፡

በዚህም ግጭት ተፈጠረ፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች የሰውዬውን ወንድም ቁርስ ብላ ብላው ከበላ በኋላ ወዲያው ሞተ ነው የሚሉት፡፡

ሐብትን አልሞ ቤቱን የሰጣት ሰውም ብዙም ሳይቆይ ከወገቡ በታች ፓራላይዝድ ሆነ፡፡ ፊዚዮቴራፒን ጨምሮ የተለያዩ ሕክምናዎች ቢሞከርም ሊድን አልቻለም ከትላንት በስቲያ አረፈ፡፡

የአካባቢው ሰው የሰውዬውን አስክሬን ወደቤት ሊያስገቡ ሲሉ፣ “ይሄ አስክሬን “ቤቴ” አይገባም” አለች ሴትየዋ፡፡ ፖሊስ ሲጠራ ከነባለቤቷ ቤቱን ጥላ መሰወሯ ተነግሯል…

ቤቱ ሲፈረሽ የተለያዩ ነገሮች ተገኝተዋል…

ሙሉውን ያዳምጡ…

Show more
Facebook Comments

Up next