ቀጥሎ የሚጫወተው


ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን በአረብ ሀገር ምን ይሰሩ ነበር !? | Ethiopia

23 ጊዜ ታይቷል
zehabesha
2
የተለቀቀበት ቀን 30 Aug 2019 / በ ዜና እና ፖለቲካ

ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን በአረብ ሀገር ምን ይሰሩ ነበር?

ከኢትዮጵያ ወደ ባሀረ ሰላጤዉ ሀገራት የሚደረገዉ ጉዞ የተጀመረዉ ገና በካራቫን የንግድ ለዉዉጥ ጊዜ በተለይም በጥንት ኢትዮጵያዊያንና በየመኖች መካከል የነበረ ቢሆንም የ21ኛዉ ክፍል ዘመን የስራ ጉዞ ግን መልኩ ባርነት እንደሆነ አያሌ ምክንያች አሉ፡፡
በተለይ ባለፉት 15 አመታት የነበረዉ የኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ የሚያደርጉት ጉዞ ሰቆቃም ዉርደትም የተቀላቀለበት ነበር፡፡

በ2009 መጋቢት ወር የሳኡዲ አረቢያ መንግስት የ90 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ኢትዮጵያዊን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ሀገሬ እንደገባችሁ ዉጡልኝ እስካለበት ጊዜ ድረስ አንድ ሽህ ኢትጵያዊያን ህጋዊም ሆነ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ በየቀኑ ከኢትዮጵያ ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ ይሰደዱ ነበር፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዞ አግዶ ቆይቷል፡፡ ያሳለፍነዉ አመት በሀገራችን የፖለቲካ ለዉጥ ሲከሰት - የለዉጡ ሀይል ከባህረ ሰላጤዉ ሀገራት ጋር የጀመረዉን ጥብቅ ወዳጅነት ተከትሎ ግን የአረብ ሀገር ጉዞ በአዲስ መልክ እንዲጀመር ተወስኗል፡፡

ለመሆኑ የዶክተር አቢይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በተለይም በቤት ሰራተኝነት የሚፈለጉ ሴቶች ወደ አረብ ሀገር አቅንተዉ እንዲሰሩ ሲፈቅድ ከዚህ ቀደም የነበረዉ የወገኖቻችን ሰቆቃ ግምት ዉስጥ ገብቷል ወይ;

ኢትዮጵዊያን ወጣቶች በአረብ ሀገራት ምን አይነት ስራ ሲሰሩ እንደነበር፣ ሲደርስባቸዉ የነበረዉን ሰቆቃም በርካቶች በተለያየ ጊዜ ቢናሩትም አንዳፍታ የዛሬዋን ባለታሪክ አናግሮ ለመጭዉ ጉዞ ትምህርት ይሆን ዘንድ በዚህ መልኩ አዘጋጅቶላችኋል፡፡

ባለታሪኳ - ፍሬህይወት ወጋየሁ ወልደ ዮሀንስ ትባላለች በሶስት የአረብ ሀገራት አስራ አንድ የስደት አመታትን አሳልፋለች፡፡ ልጆቿን በድህነት ማሳደግ - ትዳሯን ከእጅ ወደ አፍ በሆነ አቅም መምራት በነዚህ አመታት እስከዛሬ ሰምተናቸዉ የማናዉቃቸዉ አይነት ስራዎችን ስትሰራ ቆይታለች - ሰቆቃ፣ ዉርደት፣ ባይተዋርነት የተቀላቀለበት ህይወት አሳልፋለች፡፡ ይሄንን የህይወት ተሞክሮ ስታጋራን ……..
ለዉርደታችን መንስኤ የሀገራችን የስልጠና ጥራት ጉድለት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የተፈራረመዉ የሰራተኞች ዉል ደረጃ መዉረድ፣ በሀገራቱ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንፅላዎች በስራ የተጓዙ ኢትጵያዊያንን በሚገባ መብታቸዉን አለማስጠበቅ የጎላ ድርሻ አላቸዉ ባይ ነች፡፡
በስተመጨረሻም ፍሬ ህይወት አዲስ ይጀመራል የተባለዉን የአረብ ሀገር ጉዞ አስመልክቶ ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶችና ለመንግስት ምክር ለግሳለች፡፡ ሙሉዉን ዝግጅት በራሷ በባለታኳ ፍሬ ህይወት አንደበት ይከታተሉት ዘንድ ጋበዝን -

መልካም ቆይታ፡፡

ተጨማሪ አሳይ
ኮሜንት ፃፍ

ቀጥሎ የሚጫወተው