ወርቅን ጨምሮ 60 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ስር ዋበአጠቃላይ 2.45 ሚሊየን የውጭ ሀገራት ገንዘብ እና 7 ኪ.ግ ወርቅ ነው ተጠርጣሪዎቹ በቁጥትር ስር ውለዋል
0
0
93 ጊዜ ታይቷል
የተለቀቀበት ቀን 09 Feb 2019 / በ ሾው
ወርቅን ጨምሮ 60 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ስር ዋለ
***************************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትናንት ምሽት በቶጎ ዉጫሌ በጉምሩክ ሰራተኞች ወርቅን ጨምሮ 60 ሚሊየን ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተደረገ ቆጠራ መሰረት የተያዙት ገንዘቦች 1 ሚሊዮን 527ሺህ 714 የአሜሪካ ዶላር ፣ 8 ሺህ 280 ዩሮ ፣ 31 ሺህ 990 ፓዉንድ፣ 25 ሺህ 665 የካናዳ ዶላር፣ 8 ሺህ 880 የአዉስትራሊያ ዶላር፣ 1 ሺህ 393.50 ኩዬት ዲናር፣ 690 ስዊስ ፍራንክ፣ 80 ሺህ 870 ኖርዌይ ክሮዉን፣ 4 ሺህ 810 ኳታር ሪያል፣ 72 ሺህ 715 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ድርሃም፣ 904 ባህሬን ረያል፣ 734 ሺህ 088 ሱፉ ሪያል፣ 4 ኦማን ሪያል በአጠቃላይ 2.45 ሚሊየን የውጭ ሀገራት ገንዘብ እና 7 ኪ.ግ ወርቅ ነው፡፡
ገንዘቡን ሲያዘዋዉሩ የተያዙትም ተጠርጣሪዎች
1ኛ ካሚል ኡመር መሃመድ
2ኛ መሃሪ ካሪም
3ኛ መሃዲ ኡመር ኢብራሂም
4ኛ ካሊድ አብዱሳ አሊ ናቸዉ::
ተጨማሪ አሳይ
ኮሜንት ፃፍ